ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ቆሮንቶስ 3:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. እንግዲህ ይህን የመሰለ ተስፋ ስላለን፣ በድፍረት እንናገራለን።

13. እስራኤላውያን የፊቱ ማንጸባረቅ እየጠፋ ሲሄድ መጨረሻውን እንዳይመለከቱ፣ ፊቱን በጨርቅ እንደ ሸፈነው እንደ ሙሴ አይደለንም።

14. ነገር ግን ብሉይ ኪዳን በተነበበ ቊጥር ያ መሸፈኛ እስከ ዛሬ ድረስ ስላልተወገደ ልቡናቸው እንደ ደነዘዘ ነው፤ መሸፈኛው አሁንም አልተወገደም፤ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ነውና።

15. እስከ ዛሬም ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቊጥር መሸፈኛው ልቡናቸውን ይሸፍናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ቆሮንቶስ 3