ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ቆሮንቶስ 13:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኀይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።

11. በተረፈ ወንድሞች ሆይ፤ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሆኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ አንድ ሐሳብ ይኑራችሁ፤ በሰላምም ኑሩ። የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።

12. በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።

13. ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

14. የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ቆሮንቶስ 13