ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ቆሮንቶስ 11:29-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ደካማ ማን ነው? እኔስ አብሬ አልደክምምን? በኀጢአት የሚሰናከል ማን ነው? እኔስ አልቈጭምን?

30. መመካት ካለብኝ፣ ደካማነቴን በሚያሳዩ ነገሮች እመካለሁ።

31. ለዘላለም የተመሰገነው የጌታ የኢየሱስ አምላክና አባት እንደማልዋሽ ያውቃል።

32. ደማስቆ ሳለሁ ከንጉሥ አርስጦስዮስ በታች የሆነው ገዥ ሊያሲዘኝ ፈልጎ፣ የደማስቆ ሰዎችን ከተማ ያስጠብቅ ነበር።

33. ነገር ግን በግንቡ መስኮት በኩል በቅርጫት አውርደውኝ ከእጁ አመለጥሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ቆሮንቶስ 11