ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ጴጥሮስ 1:21-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. በእርሱም አማካይነት፣ ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ታምናላችሁ፤ ስለዚህ እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ላይ ነው።

22. እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን ስላነጻችሁ፣ ለወንድሞቻችሁ ቅን ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።

23. ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር ሳይሆን ሕያው በሆነና ጸንቶ በሚኖር፣ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር ነው።

24. ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል፣“ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤

25. የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”የተሰበከላችሁም የምሥራች ቃል ይህ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ጴጥሮስ 1