ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ጢሞቴዎስ 4:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እግዚአብሔርን ከማያከብር ርባናቢስ አፈ ታሪክና ከአሮጊቶች ተረታ ተረት ራቅ፤ ይልቁንም ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስህን አሠልጥን።

8. የአካል ብቃት ልምምድ ለጥቂት ነገር ይጠቅማልና፤ ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስን ማሠልጠን ግን ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁለቱም ይጠቅማል።

9. ይህ ቃል የታመነና ሙሉ ለሙሉ ሊቀበሉት የሚገባ ነው፤

10. ለዚህ ብለን እንጥራለን፤ እንደክማለንም፤ ይኸውም ለሰዎች ሁሉ በተለይም ለሚያምኑት አዳኝ በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ተስፋ ስለምናደርግ ነው።

11. እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም።

12. ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።

13. እኔ እስክመጣ ድረስ ለማንበብ፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ጢሞቴዎስ 4