ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ጢሞቴዎስ 3:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እነርሱም አስቀድመው ይፈተኑ፤ ከዚያም፣ አንዳች ነቀፋ ካልተገኘባቸው በዲቁና ያገልግሉ።

11. እንዲሁ ሴቶችም የተከበሩ፣ ሐሜተኞች ያልሆኑ ነገር ግን ልከኞችና በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባል።

12. ዲያቆናት የአንዲት ሚስት ባል መሆን ይገባቸዋል፤ ደግሞም ልጆቻቸውንና ቤተ ሰቦቻቸውን በአግባቡ የሚያስተዳድሩ መሆን አለባቸው።

13. በአግባቡ ያገለገሉ ለራሳቸው ትልቅ ክብርን፣ በክርስቶስ ኢየሱስም ባላቸው እምነት ብዙ ድፍረትን ያገኛሉ።

14. ወደ አንተ ቶሎ ለመምጣት ተስፋ ባደርግም ይህን ትእዛዝ እጽፍልሃለሁ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ጢሞቴዎስ 3