ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ጢሞቴዎስ 3:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ማንም ኤጲስቆጶስነትን ቢፈልግ፣ መልካም ሥራን ይመኛል” የሚለው ቃል የታመነ ነው።

2. እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ኤጲስቆጶስ የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልከኛ፣ ራሱን የሚገዛ፣ በሥርዐት የሚኖር፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ማስተማር የሚችል፣

3. የማይሰክር፣ የማይጣላ ግን ጨዋ የሆነ፣ የማይጨቃጨቅ፣ ገንዘብንም የማይወድ ሊሆን ይገባዋል።

4. ልጆቹን ታዛዥና አክባሪ አድርጎ በማሳደግ የገዛ ቤተ ሰቡን በአግባቡ የሚያስተዳድር ሊሆን ይገባል።

5. አንድ ሰው የራሱን ቤት ማስተዳደር ካላወቀበት፣ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊጠብቅ ይችላል?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ጢሞቴዎስ 3