ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ጢሞቴዎስ 2:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራስን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልብስ ይልበሱ እንጂ በሹሩባ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋቸው ውድ በሆኑ ልብሶች አይሽቀርቀሩ፤

10. ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ።

11. ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር።

12. ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም።

13. ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች።

14. ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ጢሞቴዎስ 2