ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ጢሞቴዎስ 2:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እኔም ለዚህ ነገር የምሥራች አብሣሪና ሐዋርያ እንዲሁም ለአሕዛብ የእውነተኛ እምነት አስተማሪ ሆኜ ተሾምሁ፤ እውነቱን እናገራለሁ፤ አልዋሽም።

8. እንግዲህ ወንዶች በሁሉም ቦታ ያለቍጣና ያለ ክርክር የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ።

9. እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራስን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልብስ ይልበሱ እንጂ በሹሩባ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋቸው ውድ በሆኑ ልብሶች አይሽቀርቀሩ፤

10. ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ።

11. ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ጢሞቴዎስ 2