ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ተሰሎንቄ 5:21-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ፤

22. ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።

23. የሰላም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ያለ ነቀፋ ይጠበቁ።

24. የጠራችሁ የታመነ ነው፤ እርሱም ያደርገዋል።

25. ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።

26. ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው።

27. ይህ መልእክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ ዐደራ እላችኋለሁ።

28. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ተሰሎንቄ 5