ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 16:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።

21. ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁላችሁ እኔ ጳውሎስ ነኝ።

22. ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታ ሆይ፤ ና!

23. የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

24. ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ነው፤ አሜን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 16