ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 16:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አሁን ደግሞ ለቅዱሳን ስለሚደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ፤ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት በሰጠሁት ትእዛዝ መሠረት አድርጉ።

2. ገንዘብ ማሰባሰብ የሚደረገው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን፣ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደ ገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ።

3. በምመጣበት ጊዜ እናንተ ለመረጣችኋቸው ሰዎች የመሸኛ ደብዳቤ ሰጥቼ ስጦታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያደርሱ እልካቸዋለሁ።

4. የእኔ መሄድ የሚያስፈልግ ከሆነ አብረውኝ ይሄዳሉ።

5. በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር፣ መቄዶንያ ከደረስሁ በኋላ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

6. ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጒዞዬ እንድትረዱኝ፣ እናንተ ዘንድ እቈይ ይሆናል፤ ምናልባትም ክረምቱን ከእናንተ ጋር እሰነብት ይሆናል።

7. አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጐበኛችሁ አልፈልግም፤ ጌታ ቢፈቅድ ረዘም ላለ ጊዜ እናንተ ዘንድ ለመሰንበት ተስፋ አደርጋለሁ።

8. ነገር ግን እስከ በዓለ ኀምሳ በኤፌሶን እቈያለሁ፤

9. ምክንያቱም ታላቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤ ብዙ ተቃዋሚዎችም አሉብኝ።

10. ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፣ አብሮአችሁ ያለ ፍርሀት እንዲቀመጥ አድርጉ፤ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና።

11. ስለዚህ ማንም አይናቀው፤ በሰላም ወደ እኔ እንዲመለስ ርዱት፤ መመለሱንም ከወንድሞች ጋር እየጠበቅን ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 16