ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 15:52-56 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

52. ይህም የሚሆነው የመጨረሻው መለከት ሲነፋ ድንገት በቅጽበተ ዐይን ነው። መለከት ይነፋል፤ ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።

53. የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።

54. የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተውም የማይሞተውን በሚለብስበት ጊዜ፣ “ሞት በድል ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።

55. እንዲሁም፣ “ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ?ሞት ሆይ፤ መንደፊያህስ የት አለ?”።

56. የሞት መንደፊያ ኀጢአት ነው፤ የኀጢአትም ኀይል ሕግ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 15