ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 12:26-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. አንድ ብልት ቢሠቃይ ብልቶች ሁሉ አብረው ይሠቃያሉ፤ አንድ ብልት ቢከብር ሌሎቹም ብልቶች አብረው ደስ ይላቸዋል።

27. እንግዲህ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የአካሉ ብልቶች ናችሁ።

28. እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንደኛ ሐዋርያትን፣ ሁለተኛ ነቢያትን፣ ሦስተኛ መምህራንን፣ ቀጥሎም ታምራት አድራጊዎችን፣ የመፈወስ ስጦታዎች ያላቸውን፣ ሌሎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፣ የማስተዳደር ስጦታ ያላቸውንና በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር ስጦታ ያላቸውን ሰዎች መድቦአል።

29. ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ መምህራን ናቸውን? ሁሉስ ታምራት ያደርጋሉን?

30. ሁሉስ የመፈወስ ስጦታዎች አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጒማሉን?

31. ነገር ግን ከሁሉ የሚበልጠውን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።ደግሞም ከሁሉ የሚበልጠውን መንገድ አሳያችኋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 12