ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 12:14-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. አካል የተሠራው ከብዙ ብልቶች እንጂ ከአንድ ብልት አይደለም።

15. እግር፣ “እኔ እጅ ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?

16. ጆሮም፣ “እኔ ዐይን ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?

17. አካል በሙሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ፣ መስማት ከየት ይገኝ ነበር? አካል በሙሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ፣ ማሽተት ከየት ይገኝ ነበር?

18. ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ እያንዳንዱን በየቦታው መድቦአል።

19. ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር?

20. እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው።

21. ዐይን እጅን፣ “አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም፤ ራስም እግርን፣ “አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም።

22. እንዲያውም ደካማ የሚመስሉት የአካል ብልቶች እጅግ አስፈላጊ ናቸው።

23. የተናቁ ለሚመስሉን ብልቶች ይበልጥ ክብር እንሰጣቸዋለን፤ ደግሞም የምናፍርባቸውን ብልቶች ይበልጥ እንንከ ባከባቸዋለን፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 12