ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 12:11-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰው እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ ይሰጠዋል።

12. አካል ብዙ ብልቶች ቢኖሩትም አንድ አካል ነው፤ ነገር ግን ብልቶች ብዙ ቢሆኑም አካል አንድ ነው። ክርስቶስም እንደዚሁ ነው።

13. አይሁድ ወይም የግሪክ ሰዎች ብንሆን፣ ባሪያ ወይም ነጻ ሰዎች ብንሆን፣ እኛ ሁላችን አንድ አካል እንድንሆን በአንድ መንፈስ ተጠምቀናልና፤ ሁላችንም አንዱን መንፈስ እንድንጠጣ ተሰጥቶናል።

14. አካል የተሠራው ከብዙ ብልቶች እንጂ ከአንድ ብልት አይደለም።

15. እግር፣ “እኔ እጅ ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?

16. ጆሮም፣ “እኔ ዐይን ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?

17. አካል በሙሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ፣ መስማት ከየት ይገኝ ነበር? አካል በሙሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ፣ ማሽተት ከየት ይገኝ ነበር?

18. ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ እያንዳንዱን በየቦታው መድቦአል።

19. ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር?

20. እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 12