ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 1:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድ ነው ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤

19. እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፤“የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤የዐዋቂዎችንም ዕውቀት ከንቱ አደርጋለሁ።”

20. ጠቢብ የት አለ? ሊቅስ የት አለ? የዘመኑስ ፈላስፋ የት አለ? እግዚአብሔር የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 1