ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዳንኤል 5:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ‘ቴቄል’ ማለት በሚዛን ተመዘንህ፤ ቀለህም ተገኘህ፣ ማለት ነው።

28. ‘ፋሬስ’ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።

29. ከዚህ በኋላ በቤልሻዛር ትእዛዝ ዳንኤልን ሐምራዊ መጐናጸፊያ አለበሱት፣ የወርቅ ሐብል በዐንገቱ ላይ አጠለቁለት፤ የመንግሥቱም ሦስተኛ ገዥ ሆኖ ተሾመ።

30. በዚያኑ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ፤

31. የሥልሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ የነበረው ሜዶናዊው ዳርዮስም መንግሥቱን ወሰደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዳንኤል 5