ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፣ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጒዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።