ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 6:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቈዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ተባዕትና እንስት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ።

20. ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ።

21. ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።”

22. ኖኅም ሁሉን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) እንዳዘዘው አደረገ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 6