ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 50:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዮሴፍ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ፣ ሳመውም።

2. ከዚያም የአባቱ የእስራኤል ሬሳ እንዳይፈርስ ባለ መድኀኒት የሆኑ አገልጋዮቹ በመድኀኒት እንዲቀቡት አዘዘ። ባለ መድኀኒቶቹም እንዳይፈርስ ሬሳውን፣ በመድኀኒት ቀቡት።

3. ሬሳው እንዳይፈርስ መድኀኒት መቀባቱ በአገሩ ልማድ መሠረት አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ግብፃውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት።

4. የሐዘኑ ጊዜ እንዳበቃ ዮሴፍ የፈርዖንን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “በፊታችሁ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩልኝ፣

5. ‘የምሞትበት ጊዜ ስለ ተቃረበ፣ በከነዓን ምድር ራሴ ቈፍሬ ባዘጋጀሁት መቃብር እንድትቀብረኝ’ ሲል አባቴ አስምሎኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ልቅበር ከዚያም እመለሳለሁ።”

6. ፈርዖንም፣ “ባስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው።

7. ከዚያም ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ወጣ፤ የፈርዖን ሹማምት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች እንዲሁም የግብፅ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 50