ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 5:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው፦እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፤

2. ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸው፤ በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው።

3. አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

4. ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤

5. አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

6. ሴት፣ ዕድሜው 105 ዓመት ሲሆን ሄኖስን ወለደ፤

7. ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

8. ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

9. ሄኖስ፣ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነ ጊዜ ቃይናንን ወለደ፤

10. ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

11. ሄኖስ በአጠቃላይ 905 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

12. ቃይናን፣ ዕድሜው 70 ዓመት ሲሆን መላልኤልን ወለደ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 5