ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 49:12-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።

13. “ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።

14. “ይሳኮር፣ ዐጥንተ ብርቱ አህያ፣በጭነት መካከል የሚተኛ፣

15. ማረፊያ ቦታው መልካም፣ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤ተገድዶም ያገለግላል።

16. “ዳን፣ ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።

17. ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 49