ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 48:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. በዚህ ጊዜ እስራኤል ዐይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ ዐቀፋቸው።

11. እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዐይንህን እንደ ገና ዐያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው።

12. ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጒልበት ፈቀቅ በማድረግ አጐንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ።

13. ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተ ቀኝ፣ ከእስራኤል በስተ ግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተ ግራ፣ ከእስራኤል በስተ ቀኝ በኩል አቀረባቸው።

14. እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፤ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኵሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ።

15. ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤“አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱየተመላለሱት እግዚአብሔር (ኤሎሂም)፣ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስበዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ (ኤሎሂም)፣

16. ከጒዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤እነርሱም በስሜ፣በአባቶቼ በአብርሃምናበይስሐቅ ስም ይጠሩ፤በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።

17. ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 48