ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 35:22-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ።ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦

23. የልያ ልጆች፦የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል፣ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤

24. የራሔል ልጆች፦ዮሴፍ፣ ብንያም፤

25. የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦ዳን፣ ንፍታሌም፤

26. የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦ጋድ፣ አሴር ናቸው።እነዚህ ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች ነበሩ።

27. ያዕቆብ አባቱ ወዳለበት ወደ መምሬ መጣ፤ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩባት፣ ቂርያት አርባቅ ወይም ኬብሮን የተባለችው ቦታ ናት።

28. ይስሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤

29. አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 35