ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 27:37-44 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. ይስሐቅም ለዔሳው፣ “በአንተ ላይ የበላይነት እንዲኖረው፣ ወንድሞቹ ሁሉ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ፣ እህሉ፣ የወይን ጠጁም የተትረፈረፈ እንዲሆንለት መርቄዋለሁ። ታዲያ ልጄ፣ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” ሲል መለሰለት።

38. ዔሳውም አባቱን፣ “አባቴ ሆይ፤ ምርቃትህ ይህችው ብቻ ናትን? እባክህ አባቴ፣ እኔንም መርቀኝ” አለው፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ።

39. አባቱ ይስሐቅም እንዲህ ሲል መለሰለት፤“መኖሪያህከምድር በረከት፣ከላይም ከሰማይ ጠል የራቀ ይሆናል፤

40. በሰይፍ ትኖራለህ፤የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ።አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ወዲያ ትጥላለህ።”

41. አባቱ ያቆብን ስለ መረቀው፣ ዔሳው በያዕቆብ ላይ ቂም ያዘ፤ በልቡም፣ “ግድ የለም፤ የአባቴ መሞቻው ተቃርቦአል፤ ከልቅሶው በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድላለሁ” ብሎ አሰበ።

42. ርብቃ፣ ታላቁ ልጇ ዔሳው ያሰበው በተነገራት ጊዜ ታናሹን ልጇን ያዕቆብን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ጊዜ እየጠበቀ ነው፤

43. አሁንም፣ ልጄ ሆይ፤ እኔ የምልህን አድርግ፤ በካራን ምድር ወደሚኖረው ወደ ላባ ቶሎ ሽሽ።

44. የወንድምህ ቍጣ እስከሚበርድ እዚያው ቈይ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 27