ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 27:29-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. መንግሥታት ይገዙልህ፤ሕዝቦችም ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤የእናትህም ልጆች ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ።”

30. ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ እንዳበቃ፣ ያዕቆብ ገና ከአባቱ ዘንድ ሳይወጣ ወዲያውኑ፣ ወንድሙ ዔሳው ከዐደን ተመለሰ።

31. እርሱም ደግሞ ጣፋጭ ምግብ በማዘጋጀት ለአባቱ አቅርቦ፣ “አባቴ ሆይ፤ እንድትመርቀኝ፣ እስቲ ቀና በልና ካደንሁት ብላ” አለው።

32. አባቱ ይስሐቅም፣ “አንተ ደግሞ ማን ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “እኔማ የበኵር ልጅህ ዔሳው ነኝ” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 27