ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 25:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የምድያም ልጆች፦ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳድ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።

5. አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤

6. ለቁባቶቹ ልጆች ግን በሕይወት እያለ ስጦታ አደረገላቸው፤ ከልጁ ከይስሐቅም ርቀው እንዲኖሩ ወደ ምሥራቅ ምድር ሰደዳቸው።

7. አብርሃም በጠቅላላው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ።

8. ከዚያም ዐረፈ፤ ዕድሜ ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።

9. ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤል በመምሬ አጠገብ በምትገኝ በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን ዕርሻ በመክፈላ ዋሻ ቀበሩት፤

10. ይህም የዕርሻ ቦታ አብርሃም ከኬጢያውያን የገዛው ነበር፤ ከሚስቱ ከሣራ አጠገብ በዚያ ተቀበረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 25