ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 16:2-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. አብራምንም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋር ተኛ” አለችው።አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ።

3. አብራም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ሚስቱ ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን አጋርን ሚስት እንድትሆነው ለባሏ ሰጠችው።

4. አብራምም ከአጋር ጋር ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች። አጋርም ነፍሰ ጡር መሆኗን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን መናቅ ጀመረች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 16