ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 14:17-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. አብራም ኮሎዶጎምርንና አብረውት የተሰለፉትን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ፣ የሰዶም ንጉሥ፣ “የንጉሥ ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።

18. የልዑል እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) ካህን የነበረው የሳሌም ንጉሥ መልከጼዴቅም እንጀራና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤

19. አብራምንም እንዲህ ሲል ባረከው፤“ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ልዑልእግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) አብራምን ይባርክ፤

20. ጠላቶችህን አሳልፎ በእጅህ የሰጠህ፣ልዑል እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) ይባረክ።”አብራምም ካመጣው ሁሉ ዐሥራትን ሰጠው።

21. የሰዶም ንጉሥም አብራምን፣ ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው።

22. አብራም ግን ለሶዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ ወደ ልዑል አምላክ (ኤል-ኤልዮን) እጆቼን አንሥቻለሁ፤

23. ‘አብራምን አበለጸግሁት’ እንዳትል፣ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ከአንተ አንዳች አልፈልግም።

24. ሰዎቼ ከበሉትና ከእኔ ጋር ከሄዱት ሰዎች ድርሻ በስተቀር ለራሴ አንዳች ነገር አልቀበልም፤ አውናን፣ ኤስኮልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 14