ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 11:18-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ፋሌቅ በ30 ዓመቱ ራግውን ወለደ፤

19. ራግውንን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

20. ራግው በ32 ዓመቱ ሴሮሕን ወለደ፤

21. ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

22. ሴሮሕ በ30 ዓመቱ ናኮርን ወለደ፤

23. ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

24. ናኮር በ29 ዓመቱታራን ወለደ፤

25. ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

26. ታራ 70 ዓመት ከሆነው በኋላ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።

27. የታራ ትውልድ ይህ ነው፦ታራ፣ አብራምን ናኮርንና ሐራንን ወለደ፤ሐራንም ሎጥን ወለደ።

28. ሐራን፣ አባቱ ታራ ገና በሕይወት እንዳለ በከለዳውያን ምድር በምትገኘው በተወለደባት ከተማ በዑር ሞተ።

29. አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ፤ የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካም የሐራን ልጅ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነበረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 11