ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 10:6-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የካም ልጆች፦ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

7. የኩሽ ልጆች፦ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።የራዕማ ልጆች፦ሳባ፣ ድዳን ናቸው።

8. ኩሽ የናምሩድ አባት ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ።

9. በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር።

10. የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በሰናዖር ምድር ነበሩ።

11. ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ረሆቦትን፣ ካለህን

12. እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ።

13. ምጽራይም፦የሉዳማውያን፣ የዕሚማውያን፣ ላህቢያውያን፣ የነፍታሌማውያን፣

14. የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የኮስሉሂማውያን፣ የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 10