ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 10:19-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።

20. እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።

21. ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔ ቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።

22. የሴም ልጆች፦ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።

23. የአራም ልጆች፦ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ናቸው።

24. አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ሳላም ዔቦርን ወለደ።

25. ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 10