ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 10:13-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ምጽራይም፦የሉዳማውያን፣ የዕሚማውያን፣ ላህቢያውያን፣ የነፍታሌማውያን፣

14. የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የኮስሉሂማውያን፣ የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።

15. ከነዓንም፦የበኵር ልጁ የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣

16. የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርሳው ያን አባት ነበረ፤

17. እንዲሁም የኤዊያውያን፣ የዑር ኬዋናውያን፣ የሲኒያውያን፣

18. የአራዴዎ ናውያን፣ የሰማሪናውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነበረ።ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤

19. የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።

20. እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።

21. ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔ ቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 10