ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 7:21-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. በአባይ ያሉት ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ከመከርፋቱ የተነሣ ግብፃውያኑ ውሃውን ሊጠጡት አልቻሉም። በግብፅ ምድር ሁሉ ደም ነበረ።

22. የግብፅ አስማተኞች በድብቅ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ፤ የፈርዖንም ልብ ደነደነ፤ ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንደ ተናገረው ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም።

23. ተመልሶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ገባ እንጂ ይህንን ከቍም ነገር አልቈጠረውም።

24. ግብፃውያን ሁሉ የወንዙን ውሃ መጠጣት ባለመቻላቸው ውሃ ለማግኘት የአባይን ዳር ይዘው ጒድጓድ ቈፈሩ።

25. እግዚአብሔር (ያህዌ) አባይን ከመታ ሰባት ቀን አለፈ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 7