ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 5:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ከፈርዖን ዘንድ እንደ ተመለሱ ሲጠብቋቸው የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አግኝተው፣

21. “እግዚአብሔር (ያህዌ) ይይላችሁ፤ ይፍረድባችሁም ፈርዖንና ሹማምንቱ እንዲጠየፉን አደረጋችሁ፤ እንዲገድሉን በእጃቸው ሰይፍ ሰጣችኋቸው” አሏቸው።

22. ሙሴም ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተመልሶ፦ “አቤቱ ጌታ (አዶናይ) ሆይ፤ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ ያመጣኸው ለምንድን ነው? የላክኽኝ ለዚሁ ነው?

23. በአንተ ስም እናገር ዘንድ ወደ ፈርዖን ከሄድሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ እርሱ በዚህ ሕዝብ ላይ፣ አበሳ አምጥቶአል፤ አንተም ሕዝብህን ከቶ አልታደግኸውም” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 5