ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 39:33-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ከዚያም የማደሪያውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡት፤ እነዚህም ድንኳንና ዕቃዎቹ ሁሉ፣ ማያያዣዎቹ፣ ክፈፎቹ፣ አግዳሚዎቹ፣ ምሰሶዎቹና መቆሚያዎቹ፤

34. ቀይ ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ የተሠራ መደረቢያ፣ የለፋ የአቆስጣ ቆዳ መደረቢያና መከለያ መጋረጃ፤

35. የምስክሩ ታቦት፣ ከመሎጊያዎቹና ከስርየት መክደኛው ጋር፤

36. ጠረጴዛው ከዕቃዎቹ ሁሉና ከኅብስተ ገጹ ጋር፤

37. ከንጹሕ ወርቅ የሆነው መቅረዝ ከተደረደሩት መብራቶችና ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፣ የመብራቱም ዘይት፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 39