ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 36:23-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. በደቡብ በኩል ላለው የማደሪያው ድንኳን ሃያ ወጋግራዎችን አበጁ፤

24. ለእያንዳንዱ ጒጠት አንድ መቆሚያ፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያ ሆኖ አርባ የብር መቆሚያዎችን አበጁ።

25. በስተ ሰሜን በኩል ላለው የማደሪያ ድንኳን ሃያ ወጋግራዎችን ሠሩ፤

26. ለእያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት መቆሚያ የሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን ሠሩ።

27. በዳር በኩል ይኸውም በስተ ምዕራብ ጫፍ ባለው ማደሪያ ድንኳን ስድስት ወጋግራዎችን ሠሩ።

28. ዳርና ዳር ላሉት የማደሪያው ድንኳን ማእዘኖችም ሁለት ወጋግራዎችን ሠሩ።

29. በእነዚህ ሁለት ማእዘኖች ላይ ከታች አንሥቶ እስከ ላይ ድረስ ወጋግራዎቹ በአንድ ላይ ተነባብረው በአንድ ቀለበት ውስጥ ተገጥመው ነበር፤ ሁለቱም አንድ አካል ሆነው ተሠርተው ነበር።

30. ስለዚህ ስምንት ወጋግራዎችና ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ሆነው ዐሥራ ስድስት የብር መቆሚያዎች ነበሩ።

31. እንደዚሁም ከግራር እንጨት አግዳሚዎችን ሠሩ፤ በማደሪያው ድንኳን በአንድ በኩል ላሉት ወጋግራዎች አምስት አግዳሚዎችን ሠሩ፤

32. በሌላ በኩል ላሉት አምስት አግዳሚዎች፣ በምዕራብ በኩል በማደሪያው ድንኳን ዳር ላይ ላሉት ወጋግራዎች አምስት አግዳሚዎችን ሠሩ።

33. በወጋግራዎቹ መካከል ከዳር እስከ ዳር እንዲዘረጋ ሆኖ መካከለኛውን አግዳሚ ሠሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 36