ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 25:28-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሥራቸው፤ በወርቅ ለብጣቸው፤ ጠረጴዛውንም ተሸከምባቸው።

29. ለመጠጥ ቍርባን መፍሰሻ ይሆኑም ዘንድ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፣ እንዲሁም ማንቆርቆሪያዎቹንና ጎድጓዳ ሳሕኖቹን ከንጹሕ ወርቅ ሥራቸው።

30. በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን ኅብስተ ገጹን በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ።

31. ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቆሚያና ዘንግ አብጅለት፤ ጽዋ መሰል አበባዎች፤ እንቡጦችና የፈነዱ አበባዎች ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ይሠሩ።

32. ከመቅረዙ ግራና ቀኝ ጎን ጋር የተያያዙ፣ በአንዱ በኩል ሦስት በሌላው በኩል ሦስት በድምሩ ስድስት ቅርንጫፎች ይኑሩት።

33. ከመቅረዙ ጋር የተያያዙት ስድስቱ ቅርንጫፎች እያንዳንዳቸው እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ሦስት ጽዋ መሰል አበባዎች፤ ጋር ያኑሯቸው።

34. በመቅረዙም ላይ አበባዎች እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው አራት የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ጽዋዎች ይኑሩ።

35. በመቅረዙ ላይ ላሉት ለስድስቱ ቅርንጫፎች እንቡጥ በመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር፣ ሁለተኛውም እንቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር፣ ሦስተኛውም እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ይሁን።

36. ዕንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከመቅረዙ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከንጹሕ ወርቅ ተቀርጸው ይሠሩ።

37. “ከዚያም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ለሚገኘው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጡ ከመቅረዙ ላይ አስቀምጣቸው።

38. መኰስተሪያና የኵስታሪ ማስቀመጫ ሳህኖቹም ከንጹሕ ወርቅ ይሠሩ።

39. ለመቅረዙና ለዕቃዎቹ ሁሉ የሚያስፈልገው አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ነው።

40. በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት መሥራትህን ልብ በል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 25