ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 25:2-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “ስጦታ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። ይሰጥ ዘንድ ልቡ ካነሣሣው ከእያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀበልልኝ።

3. ከእነርሱ የምትቀበላቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና፣ ነሐስ፣

4. ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጒር፣

5. ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የለፋ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣

6. የመብራት ወይራ ዘይት፣ ለቅብዓ ዘይቱና ጣፋጭ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፣

7. በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች።

8. “ከዚያም መቅደስ እንዲሠሩልኝ አድርግ፤ እኔም በመካከላቸው አድራለሁ።

9. ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።

10. “ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር እንጨት እንዲሠሩ አድርግ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 25