ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 22:22-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. “ባል በሞተባት ወይም አባትና እናት በሌለው ልጅ ላይ ግፍ አትዋሉ።

23. ግፍ ብትውሉባቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ፣ ጩኸታቸውን በእርግጥ እሰማለሁ።

24. ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ።

25. “ከሕዝቤ መካከል ችግረኛ ለሆነው ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁኑ፤ ወለድ አትጠይቁት።

26. የጎረቤትህን ልብስ መያዣ አድርገህ ብትይዝ ሲመሽ መልስለት፤

27. ምክንያቱም ለሰውነቱ መሸፈኛ ያለው ልብስ ያ ብቻ ነው፤ ሌላ ምን ለብሶ ይተኛል? ወደ እኔ ሲጮህ እኔ እሰማለሁ፤ እኔ ርኅሩኅ ነኝና።

28. “በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ላይ የስድብ ቃል አታሰማ፤ ወይም የሕዝብህን መሪ አትርገም።

29. “የእህልህን ወይም የወይን ጠጅህን በኵራት ለእኔ ከማቅረብ ወደ ኋላ አትበል።“የወንድ ልጆችህን በኵር ለእኔ ስጠኝ።

30. ከቀንድ ከብትህና ከበጎችህም እንዲሁ አድርግ፤ ለሰባት ቀን ከእናቶቻቸው ጋር ይቆዩ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ ሰጠኝ።

31. “እናንተ ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ የዘነጠለውን የእንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ለውሾች ስጡት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 22