ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 21:33-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. “አንድ ሰው ጒድጓድን ከፍቶ ቢተው፣ ወይም ጒድጓድ ቆፍሮ ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣

34. የጒድጓዱ ባለቤት ኪሳራ ይክፈል፤ ለባለቤቱ መክፈል አለበት፤ የሞተውም እንስሳ ለእርሱ ይሆናል።

35. “የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድለው፣ በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው ገንዘቡንና የሞተውን እንስሳ እኩል ይካፈሉ።

36. ሆኖም በሬው የመዋጋት ዐመል ያለው መሆኑ ከታወቀ፣ ባለቤቱም በረት ሳይዘጋበት ቢቀር፣ ባለቤቱ በሬውን በበሬው ፈንታ ይክፈል፤ የሞተውም እንስሳ ለእርሱ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 21