ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 21:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እነዚህን ሦስት ነገሮች የማያሟላላት ቢሆን፣ ያላንዳች የገንዘብ ክፍያ በነጻ መሄድ ይኖርባታል።

12. “ሰውን ደብድቦ የገደለ ሞት ይገባዋል።

13. ሆኖም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፈቅዶ ሰውየው ሳያውቅ በድንገት አድርጎት ከሆነ፣ እኔ ወደምወስነው ስፍራ ይሽሽ።

14. አንድ ሰው በተንኰል ሆን ብሎ ሌላውን ቢገድል፣ ከመሠዊያዬ ተወስዶ ይገደል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 21