ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 15:8-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ውሆች ተቈለሉ፤ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።

9. “ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፤እማርካቸዋለሁ፤ምርኮን እካፈላለሁ፤ነፍሴ በእነርሱ ትጠግባለች፤ሰይፌን እመዛለሁ፤እጄም ትደመስሳቸዋለች አለ።

10. አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ባሕርም ከደናቸው፤በኀያላን ውሆች፣እንደ ብረት ሰጠሙ።

11. “አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ከአማልክት መካከል፣ እንደ አንተ ማን አለ?በቅድስናው የከበረ፣በክብሩ የሚያስፈራ፣ድንቆችን የሚያደርግ፣እንደ አንተ ማን አለ?

12. ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ምድርም ዋጠቻቸው።

13. ‘በማይለወጠው ፍቅርህ፣የተቤዥሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤እነርሱን በብርታትህ፣ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 15