ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 15:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘመሩ፤“ከፍ ከፍ ብሎ ከብሮአልና፣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) እዘምራለሁ፤ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣በባሕር ውስጥ ጥሎአልና።

2. ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ድነቴም ሆነልኝ፤እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

3. ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።

4. የፈርዖንን ሠረገሎችና ሰራዊት፣ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ምርጥ የሆኑት የፈርዖን ሹማምት፣ቀይ ባሕር ውስጥ ሰጠሙ።

5. ቀላያትንም ለበሱ፤እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረዱ።

6. “አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ቀኝ እጅህ በግርማ ከበረ፤አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ቀኝ እጅህ ጠላትን አደቀቀ።

7. በግርማህ ታላቅነት፣የተቃወሙህን ጣልኻቸው፤ቍጣህን ሰደድህ፤እንደ ገለባም በላቸው።

8. በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ውሆች ተቈለሉ፤ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።

9. “ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፤እማርካቸዋለሁ፤ምርኮን እካፈላለሁ፤ነፍሴ በእነርሱ ትጠግባለች፤ሰይፌን እመዛለሁ፤እጄም ትደመስሳቸዋለች አለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 15