ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 13:2-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “መጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከእስራኤላውያን መካከል የእናቱ የበኵር ልጅ የሆነው ማሕፀን ከፋች ሰውም ሆነ እንስሳ የእኔ ነው።”

3. ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ምድር ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ዕለት አስታውሱ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር (ያህዌ) በኀያል ክንዱ አውጥቶአችኋል። እርሾ ያለበትን ማንኛውንም ነገር አትብሉ።

4. እነሆ በዚች ዕለት በአቢብ ወር ወጥታችኋል።

5. እግዚአብሔር (ያህዌ) ለእናንተ ለመስጠት ሲል ቀድሞ ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ኤዊያውያን፣ ኢያቡሳውያን ምድር በምትገቡበት ጊዜ ይህን በዓል በዚህ ወር ታከብራላችሁ።

6. ለሰባት ቀን ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ትበላላችሁ። በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በዓል ታደርጋላችሁ።

7. በእነዚህም ሶስት ቀናት ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ እርሾ ያለበት ነገር ፈጽሞ አይገኝ፤ በምድራችሁም አዋሳኝ በየትኛውም ቦታ እርሾ ፈጽሞ አይኑር።

8. በዚያችም ዕለት፣ ‘እኔ ይህን የማደርገው ከግብፅ ምድር በወጣሁበት ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) ስላደረገልኝ ነገር ነው’ ብለህ ለልጅህ ንገረው።

9. የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሕግ በከንፈራችሁ ላይ እንዲሆን ይህ በዓል ለእናንተ በእጃችሁ ላይ እንደ ታሰረ ምልክት፣ በእግራችሁ ላይ እንደሚገኝ መታሰቢያ ይሆንላችኋል። እግዚአብሔር (ያህዌ) በኀያል ክንዱ ከግብፅ አውጥቶአችኋልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 13