ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 6:17-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሰጣችሁን ትእዛዞች፣ መመሪያዎችና ሥርዐቶች በጥንቃቄ ጠብቁ።

18. መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤

19. እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረትም ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ታስወጣለህ።

20. በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ “አምላካችን እግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሂም) ያዘዛችሁ የመመሪያዎቹ፣ የሥርዐቶቹና የሕጎቹ ትርጒም ምንድ ነው?” ብሎ በሚጠይቅህ ጊዜ፣

21. እንዲህ በለው፤ “እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሮች ነበርን፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን በብርቱ እጅ ከግብፅ አወጣን።

22. እኛ በዐይናችን እያየን እግዚአብሔር (ያህዌ) ታላላቅና አስፈሪ የሆኑ ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆችን በግብፅ፣ በፈርዖንና በመላው ቤተ ሰዎቹ ላይ አደረገ።

23. እኛን ግን ለአባቶቻችን በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ሊያስገባንና ሊሰጠን ከዚያ አወጣን።

24. ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንልንና በሕይወት እንድንኖር ይህን ሥርዐት ሁሉ እንድንፈጽም፣ አምላካችንንምእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) እንድንፈራ እግዚአብሔር (ያህዌ) አዘዘን።

25. እንግዲህ ይህን ሁሉ ሕግ እርሱ ባዘዘን መሠረት፣ በአምላካችንበእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ተጠንቅቀን ከጠበቅን፣ ያ ለእኛ ጽድቃችን ይሆናል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 6