ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 33:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰጠው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው፤

2. እንዲህም አለ፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሲና መጣ፤በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሓይ ወጣ፤ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጣ፤በስተ ቀኙ የሚነድ እሳት ነበር።

3. በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው።ከእግርህ ሥር ሁሉ ይሰግዳሉ፤ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤

4. ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ፣የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።

5. የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፣በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።

6. “ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት፤የወገኖቹ ቊጥርም አይጒደልበት።”

7. ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ወደ ወገኖቹም አምጣው።በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!

8. ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦“ቱሚምህና ኡሪምህ፣ለምትወደው ሰው ይሁን፤ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።

9. ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፣‘ስለ እነርሱ ግድ የለኝም’ አለ።ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ልጆቹንም አላወቃቸውም።ለቃልህ ማን ጥንቃቄ አደረገ፤ኪዳንህንም ጠበቀ።

10. ሥርዐትህን ለያዕቆብ፣ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል።ዕጣን በፊትህ፣የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በመሠዊያህ ላይ ያቀርባል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 33