ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 32:14-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ማለፊያውንም የወይን ጠጅ፣

15. ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤የፈጠረውንም አምላክ (ኤሎሂም) ተወ፤መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ።

16. በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤በአስጸያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቈጡት።

17. አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፦ላላወቋቸው አማልክት፣ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፣አባቶቻችሁ ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ።

18. አባት የሆነህን ዐለት ከዳኸው፤የወለደህን አምላክ (ኤሎሂም) ረሳኸው።

19. እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን አይቶ ናቃቸው፤በወንድና በሴት ልጆቹ ተቈጥቶአልና።

20. እርሱም፣ “ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤”“መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ አለ፤ጠማማ ትውልድ፣የማይታመኑም ልጆች ናቸውና።

21. አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤በከንቱ ጣዖቶቻቸው አስቈጡኝ።እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ።በማያስተውልም ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ።

22. በቊጣዬ እሳት ተቀጣጥሎአልና፤እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነዳል።ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 32