ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 32:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሰማያት ሆይ፤ አድምጡ፤ እኔም እናገራለሁ፤ምድር ሆይ፤ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ።

2. ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።

3. እኔ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ዐውጃለሁ፤የአምላካችንን (ኤሎሂም) ታላቅነት አወድሱ!

4. እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም (ኤሎሂም) እርሱ ነው።

5. በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው።

6. አንተ ተላላና ጥበብ የጐደለህ ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) የምትመልስለት በዚህ መንገድ ነውን?አባትህ ፈጣሪህ፣የሠራህና ያበጀህ እርሱ አይደለምን?

7. የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 32